About Us
Company Profile
Company Profile
የኢትዮ ሬል ሎጅስቲክስ ኃ.የተ.የግ.ማ (ERL) ሶሉሽንስ ተለዋዋጭነት ያለው እና የራሱ መርከብ የሌለው ባለብዙ-አይነት (Multimodal) የትራንስፖርት ኦፕሬተር (NVOCCMTO) ነው። ከጫፍ እስከ ጫፍ አለም አቀፍ የሎጂስቲክስ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ በተለይም የውቅያኖስ ጭነትንና የተቀናጀ ባለብዙ-ቅርጽ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን በማቅረብ የተካነ ነው። ንግዶችን ከአለም ጋር ለማገናኘት ሙያዊ እውቀታችንን እና ግንኙነታችንን እንጠቀማለን፣ ለጠቅላላ የአቅርቦት ሰንሰለት ፍላጎት ለማሟላት የአንድ መስኮት አገልገሎት እናቀርባለን።በኢትዮጵያ ከመርከብ አልባ ባለብዙ-አይነት የትራንስፖርት ኦፕሬተርነት (MVOCCC) ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሚያወጧቸዉን ሁሉንም ህጋዊ መስፈርቶች እና ደንቦች አንዲሁም ፈቃዶችን በጥብቅ እንከተላለን። በአደገኛ ቁሶች ላይ ያሉ እንደ የማቴሪያል ማስታወቂያ (MDs) እና የአቅራቢው የተስማሚነት ማረጋገጫ (SDoCs) ያሉ የጭነት ሰነዶች ትክክለኛ እና የተሟሉ መሆናቸውን እናረጋግጣለን።የደንበኞቻችን ምርቶች እና ሎጂስቲክስ እንደ SOLAS እና MARPOL ከመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ደንቦች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን እናረጋግጣለን።ከመርከብ ተገዢነት እና አስፈላጊ ተያያዥ መረጃዎች ሃላፊነት ካለባቸው መርከብ ኦፕሬተሮች ጋር በመስራት ጭነታቸው በትክክል መያዙን እናረጋግጣለን።